=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
.♥.ከወደክበት ነገር ተወሽቀህ መቅረት ሳይሆን ከውድቀትህ ተምረህ ነገሮችን ለማሻሻል ሞክር!!!.♥.
ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ እንደሚታወቀው የዚች አለም ኑሮ ጊዜያዊና ጠፊ ነው። ታዲያ እኛ ደግሞ ዝምብለን አልተፈጠርንም። ማለቴ አሏህ በቁርአኑ እንደገለፀው እኛ የተፈጠርንበት አላማ አሏህን በብቸኝነት ልንገዛ ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ አሏህን በብቸኝነት ለመገዛት ፣ እምነታችነን ሙሉ ለማድረግ እውቀት የመልካም ስራዎቻችን የጀርባ አጥንት በመሆኑ ዛሬ ላይ የእውቀት የመሠረት ዲንጋይ ልንጥል ግድ ነው። ይህን ለማድረግ አላማችነን መንደፍና ጊዜያችነን ከፋፍለን መጠቀም ይኖርብናል።
ውድ እህት ወንድሞቼ ሆይ! ግባችንን ከመንደፋችን እና ጊዜያችነን ከፋፍለን ከመንቀሳቀሳችን ጋራ ተያይዞ አንድ ልናውቀው የሚገባ ነገር አለ። ይህም ግባችነን ለማሳካት በምንጥርበት ጊዜ ከተለያየ አቅጣጫ መሠናክል ሊገጥመን እንደሚችል አስቀድመን ልናውቅና እነዚህን መሠናክሎች(የለውጥ ማነቆዎችን) እንዴት በስኬት ማለፍ እንደምንችል ልናውቅ ይገባል። በተለይ ወጣቶች በመሆናችን ከጏደኞቻችን ትልቅ ተፅእኖ ሊያጋጥመን ስለሚችል ይህን ተፅእኖ መልካምና መጥፎ ጐኑን ገምግመን ከኛ እቅድ ጋር የሚቃረን ከሆነ ለተፅእኗቸው ጋሻ ለናበጅለት ይገባል።
☀:."•..♥♥ግብክን ለማሳካት ስትንቀሳቀስ ውድቀት ቢያጋጥምህና የተስፋመቁረጥ ስሜት ቢሰማህ ራዕይህን እውን የምታደርግባቸው ከ10 በላይ መንገዶች አሉና አትዘን!!!♥♥."•..☀:.
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|